የማይቻለውን መቻል
በእኛ የህይወት ዘመን፣ ተመራማሪዎች እንደ ሂውማን ፓፒሎማቫይረስ (ኤችፒ) እና ሄፓታይቲስ ሲ ለመሳሰሉ በሽታዎች መድሃኒት አግኝተዋል። ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ጤናማ ህይወት መምራት ችለዋል። ፖሊዎ ከምድር ጠፍቷል። ይህ ሁሉ የሆነው በጤና ምርምሮች አማካኝነት ነው።
በምርምር ጥናቱ ለመሳተፍ እያሰቡ ነው? በመጀመሪያ ሲታሰብ፣ የምርምር ጥናት ውስጥ መሳተፍ ለጉዳት ሊያጋልጥ የሚችል እና ግራ የሚያጋባ ሊሆን ይችላል። የእርስዎን ደህንነት ለመጠበቅ ምን አይነት ጥንቃቄ እንደሚደረግ እርስዎ ሂደቱን እንዲረዱት ለማድረግ ይህ መረጃ ሰጪ ይዘት ተዘጋጅቷል።
ለመጀመር፣ የምርምር ጥናት ሲባል ምን ማለት ነው?
የምርምር ጥናት ሲባል በሽታን እንዴት መከላከል፣ መመርመር፣ ማዳን እና ማከም እንደሚቻል አዳዲስ ሃሳቦችን እና ህክምናዎችን የመሞከር ሂደት ነው። ለእያንዳንዱ ጥናት ሃላፊነት የሚወስድ ሰው የሚኖር ሲሆን ይህ ሰው ብዙ ጊዜ ዋና ተመራማሪ በሚል የሚጠራ ሐኪም ይሆናል። ዋና ተመራማሪው ለሙከራው ዕቅድ የሚያወጣ ሲሆን ይህ ዕቅድም ፕሮቶኮል በሚል ይታወቃል። ፕሮቶኮሉ በሙከራው ጊዜ ምን እንደሚከናውን ያብራራል። በተጨማሪም ይህ ጥናት ለእርስዎ ትክክለኛ ስለመሆኑ ሀኪሙ እንዲረዱ የሚያግዝ መረጃ አለው (www.cancer.gov)።
ምርምር የማድረግ ጥቅሞች ምንድን ናቸው?
የተወሰኑ ሰዎች አዳዲስ ህክምናዎችን በእራሳቸው ላይ ለመሞከር በምርምር ተሳታፊ ይሆናሉ። ሌሎች ሰዎች ደግሞ ወደፊት በጤና ላይ ሊኖር በሚችል ማሻሻያ ላይ እገዛ ለማድረግ በምርምር ተሳታፊ ይሆናሉ። እርስዎም ልዩነት መፍጠር ይችላሉ!
ተመራማሪዎች የእኔን ደህንነት የሚጠብቁት እንዴት ነው?
በምርምር ጥናቱ ተሳታፊ ለመሆን የተወሰነ ማንገራገር ሊኖርዎት ይችላል። የምርምር ጥናቶች በተሳታፊዎች፣ በተለይ ደግሞ በነፍሰጡሮች እና በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ በመሳሰሉ ለጥቃት ተጋላጭ ግለሰቦች ላይ ያላግባብ እንዳይጠቀሙ የሚከላከሉ በርካታ ህጎችና ደንቦች አሉ። IRB (ኢንስቲቲዩሽናል ሪቬው ቦርድ)፣ ሀኪሞንች፣ የስነ-ምግባር ባለሙያዎችንና የበሽተኞች ደህንነት ተሟጋቾችን ያቀፈ ቡድን በመመስረት የምርምር ጥናቱን ይገመግማል። የምርምር ጥናቱ በሰዎች ላይ ያላግባብ ተጠቃሚ እንዳይሆን IRB ሃላፊነት አለበት። ይህም በሙከራው ተሳታፊ የሚሆኑ ሰዎች ፈቃደኛ መሆናቸውን እና በማንኛውም ጊዜ ምንም ምክንያት ማቅረብ ሳይጠበቅባቸው ከሙከራው እራሳቸውን ማግለል የሚችሉ መሆኑን ስለመረዳታቸው ማረጋገጥን ይጨምራል። በተጨማሪም ሙከራው በሚካሄድበት ጊዜ ሁሉ ተሳታፊዎች ምን እየተከናወነ እንደሆነ ማወቅ እንዲችሉ IRB በቦታው ይገኛሉ።
ሁሉም የምርምር ጥናቶች መድሃኒት ያለባቸው ናቸው?
አይ፣ የምርምር ጥናቱ የአካል እንቅስቃሴን፣ የምግብ ለውጥ ማድረግ አንዳንድ ጊዜም መጠይቅ መሙላት ሊሆን ይችላል።
መድሃኒትን ያካተቱ የምርምር ጥናቶች በአራት ክፍሎች ይከፈላሉ።
ክፍል 1፦ ይህ ክፍል በሰዎች ላይ ጥቅም ላይ ሲውል ለመጀመሪያ ጊዜ በሚሆንበት ጊዜ ሲሆን፣ የሚወሰደውም በጣም በአነሰ መጠን ነው። ይህ ክፍል በዋናነት የሚያተኩረው ሰውነት ለመድሀኒቱ የሚሰጠውን ምላሽ በማጥናት ላይ ነው። በዚህ አይነት ጥናት ወደ አስራ ሁለት ሰዎች ያህል ይሳተፋሉ።
ክፍል 2፦ ይህ ክፍል ትኩረት የሚያደርገው የመድሃኒቱን ውጤታማነት በመለካት ላይ ሲሆን ከ25-100 የሚሆኑ በርከት ያሉ ተሳታፊዎች ይሳተፉበታል።
ክፍል 3፦ የክፍል 3 ዓላማ እንደ አዲስ የተሞከረው መድሃኒት በመደበኛነት ሰዎችን ለማከም ጥቅም ላይ ከሚውለው መድሃኔት አኳያ የተሻለ ስለመሆኑ ለማወቅ ነው። በዚህ ደረጃ ያለ ክሊኒካል ሙከራ ቢያንስ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የሚኖሩት ሲሆን ረዘም ያለ ጊዜም ሊወስድ ይችላል።
ክፍል 4፦ ክፍል 4 ላይ ያሉ መድሀኒቶች ቀድሞውኑ በFDA ፈቃድ ያገኙ ሲሆኑ፣ ይህ ማለት መድሃኒቱ ለታሰበው ማህበረሰብ ከሚያመጣው የታወቀ ጉዳት በላይ የሚሆን ጥቅም የሚሰጥ ነው (www.fda.gov)። ብዙ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ይኖሩታል። በዚህ ደረጃ ያሉ መድሀኒቶች በእረጅም ጊዜ የሚኖራቸው ተፅዕኖ ይጠናል።
የምርምር ጥናት ተሳታፊ መሆን ያለብኝ ለምንድን ነው?
ዛሬ፣ ሰዎች የተሻለ ህይወት የሚመሩት ባለፉት ጊዚያት በተደረጉ የምርምር ጥናቶች ውጤት ነው። በምርምር ጥናቶች፣ ሀኪሞች አዳዲስ ዘዴዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ውጤታማ እንደሆኑ እንዲሁም አሁን ካሉ ዘዴዎች የተሻሉ እንደሆኑ ለማወቅ ያስችሏቸዋል። በምርምር ጥናቶች ሲሳተፉ፣ ለወደፊት በሽተኞች እኛ የሚኖረንን እውቀት ይጨምራሉ። የምርምር ጥናቶች የጤና ሁኔታን ለማሻሻል ቁልፍ አጋዦች ናቸው። (www.cancer.gov)። ጤናማ ቢሆኑም ወይም የህክምና ሁኔታ ቢኖርብዎትም፣ በምርምር ጥናት የእርስዎ ተሳትፎ በህክምናው ዘርፍ ጉልህ አስተዋጽዖ ሊያደርግ ይችላል።
በምርምር ጥናቱ እንዴት መካተት እችላለሁ?
ለዚህ የተዘጋጀ ResearchMatch በመባል የሚታወቅ መገልገያ በመጠቀም የምርምር ጥናቶችን መፈለግ ይችላሉ። ResearchMatch ነጻ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መመዝገቢያ ነው። Research Match ከመጠይቆች እስከ የክሊኒክ ሙከራዎች ድረስ እርስዎን "ለማዛመድ" የሚያግዝዎት ሲሆን፣ ሁልጊዜም ቢሆን መሳተፍ የሚፈልጉትን ነገር የመምረጡን እድል ለእርስዎ ይሰጥዎታል።
ለተጨማሪ መረጃ፣ ከታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ።